ይህ መርጃ መስማት የተሳናቸው እና ለመስማት ከሚቸገሩ ግለሰቦች ጋር በሚገናኙበት ጊዜ የቴሌኮሙኒኬሽን ማስተላለፊያ አገልግሎት (TRS) ወይም TTY (የጽሑፍ ስልክ) ማሽንን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ መመሪያ ይሰጣል።
TTY (የጽሑፍ ስልክ/TDD) ምንድን ነው?
የጽሑፍ ስክሪን ያለው የመተየቢያ ቁልፍ ሰሌዳን ይመስላል፣ TTY መስማት የተሳነውን፣ ለመስማት የሚቸገርን ወይም የንግግር ችግር ያለበት ግለሰብ የስልክ ጥሪዎችን እንዲያደርግ እና ለመቀበል ያስችላል። ውይይቱ የሚነበበው በብርሃን ማሳያ ስክሪን እና/ወይም በወረቀት ህትመት በ TTY ላይ ነው። TTY የሚጠቀሙ ሰዎች በቴሌኮሙኒኬሽን ማስተላለፊያ አገልግሎት በኩል ወደ ማንኛውም መደበኛ የስልክ ተጠቃሚ ሊደውሉ ይችላሉ ወይም በቀጥታ ወደ ሌላ የ TTY ተጠቃሚ ሊደውሉ ይችላሉ።
ሁለት አጠቃላይ የ TTY ዓይነቶች አሉ። የድምጽ TTYዎች የ TTY ጥሪ ለመቀበል ወይም ለማድረግ መደበኛ የስልክ ቀፎ የሚቀመጥባቸው ኩባያዎች አሏቸው። የቀጥተኛ ግንኙነት TTYዎች በቀጥታ ከስልክ መስመር ጋር የተገናኙ ናቸው።
TTY መጠቀም
በ TTY ለመግባባት፣ ለመላክ የሚፈልጉትን መልዕክት በTTY ቁልፍ ሰሌዳ ላይ ይተይቡ። ሲተይቡ፣ ሲያወሩ ድምፅዎ በስልክ መስመር እንደሚላክ ሁሉ መልዕክቱ በስልክ መስመር ይላካል። የሌላውን ሰው ምላሽ በ TTY የጽሁፍ ማሳያ ላይ ማንበብ ይችላሉ።
የቴሌኮሙኒኬሽን ማስተላለፊያ አገልግሎትን መጠቀም - 711
TTY ከሌለዎት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ማስተላለፊያ አገልግሎትን (TRS) በመጠቀም መስማት የተሳነው፣ ለመስማት የሚቸገር ወይም የንግግር ችግር ወዳለበት ሰው መደወል ወይም ጥሪዎችን መቀበል ይችላሉ። በ TRS፣ የሚደውሉለት ሰው ቃላቶችዎን በ TTY ማሳያው ላይ ማንበብ እንዲችል አንድ ኦፕሬተር የሚናገሩትን ሁሉ ይጽፋል። እሱ ወይም እሷ ምላሹን መልሰው ይተይባሉ፣ ይህም የ TRS ኦፕሬተር በስልክ እንዲሰሙ ጮክ ብሎ ያነብልዎታል። በተጨማሪም የ "IP" ማስተላለፊያዎች አሉ፣ ለዚህም አካል ጉዳተኛ ሰው በበይነመረብ ላይ የእነሱን ንግግር ለኦፕሬተር ለመፃፍ ኮምፒውተር ይጠቀማል።
ከክፍያ ነፃ የ TRS አገልግሎቶች በቀን 24 ሰዓት፣ በዓመት 365 ቀናት ይገኛሉ። በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በማንኛውም ቦታ ከ TRS ጋር ለመገናኘት ወደ 711 መደወል ይችላሉ።
ባህላዊ የ TTY ጥሪዎችን ለማድረግ የሚያገለግል መመሪያ
- የስልክ ቀፎውን በ TTY የድምጽ ማጣመሪያ (ሞደም) ውስጥ ያስቀምጡ እና ሃይሉን ያብሩ። ሁለት ትናንሽ መብራቶች ይመጣሉ። የኃይል መብራቱ ብቻ ነው የሚቆየው፦ የስልኩ መብራቱ በድምጽ ማጣመሪያ ለሚነሱት ማናቸውም ድምፆች ምላሽ ለመስጠት ይጠብቃል።
- ወደ ስልክ ቁጥሩ ይደውሉ እና የ TTY መብራቱን ይመልከቱ፣ ይህም የመደወያ ስልክ ምልክቶች፣ የተጨናነቀ ምልክትን ወይም በተዛማጅ የብርሃን ቅጦች የስልክ ጥሪን ያሳያል። መብራቱ ለድምፅ ርዝመት በርቶ ይቆያል እና ድምጽ በማይኖርበት ጊዜ ይጠፋል። ለምሳሌ፣ መብራቱ በተጨናነቀ ምልክት በፍጥነት እና ምቱን ጠብቆ ያበራል።
- ለ TTY መልስ የሚሰጠው ሰው ከስሙ ወይም ከስሟ እና አጭር መልዕክት ጋር እንዲሁም “GA” ማለትም “ቀጥል” የሚል ቃል በማስከተል የአጭር መልዕክት ምላሽ ይሰጣል።
- በዚህ ጊዜ መተየብ ይጀምራሉ እና እራስዎን ያሳውቃሉ።
- የውይይቱን ተራ ለማቆም ፣ “GA” ብለው ይተይቡ እና ሌላኛው ሰው እንደገና መተየብ ይጀምራል። እያንዳንዱ ሰው ተራውን መውሰድ የሚጠበቀው ከሌላኛው ወገን “GA” ከተቀበለ በኋላ ብቻ ነው።
- ንግግርዎን ከጨረሱ በኋላ በT TY ላይ ማውራት እንደጨረሱ ግለሰቡ እንዲያውቅ ለማድረግ “GA to SK” ብለው ይተይቡ፣ ትርጉሙም “በመጨረሻ የሚናገሩት ካለ ይቀጥሉ” ወይም "ደህና ይሁኑ" ማለት ነው።
- በሂደት ላይ ያለ የ TTY መልዕክት፣ አንድ ሰው ሌላው ሰው እንደሚተይብ ቢያውቅ እንኳን ሊቋረጥ አይችልም።
- የ TTY እና TTY የማስተላለፊያ ጥሪዎች ከድምጽ ጥሪዎች ትንሽ ረዘም የሚል ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ። እባክዎ ይታገሱ።
የ TTY ስነ ምግባር
- ለ TTY ተጠቃሚዎች ሲደውሉ፣ ስልኩ ከመዘጋቱ በፊት ቢያንስ 7 ወይም ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ እንዲደውል ያድርጉ። ብዙ የ TTY ተጠቃሚዎች ለሚደወሉ ስልኮች እንዲያነቋቸው ብልጭ የሚሉ መብራቶች ላይ ይተማመናሉ። መብራቶች ትኩረትን ለመሳብ ከድምጽ የበለጠ ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ።
- ደዋዮች በጥሪዎች መጀመሪያ ላይ እራሳቸውን ማሳወቅ አለባቸው። ውይይቱን የሚመለከቱ ሌሎች ሰዎችም መታወቅ አለባቸው።
- ጥሪዎች “ይጠብቁ” ላይ ሲሆኑ ወይም ሲተላለፉ ሁልጊዜ ለ TTY ተጠቃሚዎች ይንገሩ።
- የ TTY ተጠቃሚዎች “ታነበኛለህ?” ብለው ሲተይቡ መልዕክቱ ግልጽ መሆኑን እና ከተዛቡ ቃላት እና ቁጥሮች ውጭ መሆን አለመሆኑን ማወቅ ይፈልጋሉ። መልዕክቱ የተዛባ ከሆነ፣ የክፍት ቦታ ቁልፉን ጥቂት ጊዜ ይምቱ። ይህ መልዕክቱን ካላብራራው፣ ሁለቱም ወገኖች ስልኩን ዘግተው ጥሪውን እንደገና መሞከር አለባቸው።
ጊዜ ቆጣቢ ፈጣን ምክሮች
ጊዜን ለመቆጠብ፣ የተለመዱ የእንግሊዘኛ ምህጻረ ቃላት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ይውላሉ። በተጨማሪም፣ አንዳንድ ሥርዓተ-ነጥብ፣ መጣጥፎች ወይም መስተዋድዶች በትርጉም ውስጥ ጣልቃ በማይገቡበት ጊዜ ተትተዋል።
የተለመዱ የ TTY ምህጻረ ቃላት
GA | "ይቀጥሉ" |
U | "እርስዎ" |
XXX | "ስህተት" |
HD | "ይጠብቁ" |
Q | "የጥያቄ ምልክት ወይም "?" |
MSG | “መልዕክት” |
THX | "አመሰግናለሁ" |
TMW | "ነገ" |
BEC ወይም CUZ | "ምክንያቱም" |
SK | “በመጨረሻ የሚናገሩት ካለ” ወይም "ደህና ይሁኑ" |
GA ወይምSK | "ሁሉንም መልዕክቶች ማጠናቀቅ እና ስልኩን ለማቋረጥ መዘጋጀት" |