የተልዕኮ መግለጫ
የዲሲ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ (ODR) ተልእኮ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሚተዳደሩ ወይም የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው ፕሮግራሞች፣ አገልግሎቶች፣ ጥቅማጥቅሞች፣ ተግባራት እና ተቋማት በአካል ጉዳተኛ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ተደራሽ እና ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው። ODR አካል ጉዳተኞችን ለማካተት፣ ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶች ለመስጠት እና የራሳቸውን እድል በራሳቸው እንዲወስኑ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው። ODR በአካል ጉዳተኛ አሜሪካውያን ህግ (ADA) እና ሌሎች የአካል ጉዳተኝነት መብቶች ህጎች መሰረት የከተማዋን ግዴታዎች አፈፃፀም እንዲቆጣጠር በዲሲ ምክር ቤት እና ከንቲባ ተሹሟል።
የ ODR አገልግሎቶች
- የመድልዎ ቅሬታዎችን መመርመር።
- ለዲስትሪክት ኤጀንሲዎች የ ADA ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ።
- የኤጀንሲዎችን የ ADA ዕቅዶች በመከታተል በዲስትሪክቱ መንግሥት ውስጥ የ ADA ተገዢነትን መቆጣጠር።
- በኤጀንሲዎች ከተሾመ የ ADA አስተባባሪ ጋር መስራት።
- Olmstead (የማህበረሰብ ውህደት) እቅድ ማውጣት::
- የዲስትሪክት አካል ጉዳተኛ ሰዎችን ተደራሽነት ለማሻሻል የፖሊሲ እና የበጀት ምክረ ሃሳቦች።
ODR ለዲሲ የእድገት እክሎች ምክር ቤት (DDC) የተሾመ የግዛት ኤጀንሲ (DSA) ሆኖ ያገለግላል፣ ይህ ማለት የ DDC ሰራተኞች በ ODR የህዝብ ስም ዝርዝር ውስጥ የቀረቡ ሲሆን ODR የ DDC በጀት እና ከፕሮግራም ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን ለከንቲባው የማቅረብ ሃላፊነት ተጥሎበታል።