Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

odr

Office of Disability Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

የብሬይል አገልግሎቶች የአስተርጓሚ ፕሮግራም

Braille Services Interpretation Program

የብሬይል ቋንቋ አስተርጓሚ መቼ እንደሚጠየቅ፦

  • የዲስትሪክቱ ነዋሪ ወይም የዲሲ የመንግስት ኤጀንሲ ደንበኛ/ሸማች ይፋዊ የዲሲ የመንግስት የማስረጃ ጽሁፎችን በተለዋጭ ቅርፀቶች (ብሬይል፣ ትልቅ ህትመት) ሲጠይቁ።
  • የታተሙ የማስረጃ ጽሁፎች ብቸኛ የመገናኛ ዘዴዎች ሲሆኑ ማየት የተሳናቸው ወይም ዝቅተኛ የማየት ችሎታ ያላቸው ሰዎች ከዲስትሪክቱ የመንግስት አገልግሎቶች ተጠቃሚ መሆን መቻላቸው አስፈላጊ ነው።
  • የዲስትሪክት መንግስት ማየት የተሳናቸው ወይም ዝቅተኛ የማየት ችሎታ ያላቸው ግለሰቦች ከኤጀንሲዎች ይፋዊ ሰነዶችን እንዲጠይቁ እና ከ 5-7 ባሉት የስራ ቀናት ማስታወቂያ መስጠት እንዳለባቸው ለመምከር የአሰራር ዘዴ ማቅረብ አለበት።

ይፋዊ የዲስትሪክት የመንግስት የጽሁፍ ማስረጃ ማስታወቂያዎች እና የድረ ገጽ ልጥፎች የሚከተሉትን ሊያመለክቱ ይገባል፦ "ሰነዶች ሲጠየቁ በብሬይል ቋንቋ ሊቀርቡ ይችላሉ። ሰነዱን በብሬይል ለመጠየቅ እባክዎን ለ[የኤጀንሲው አድራሻ ሰው እና የመገኛ መረጃ] ያሳውቁ።"

አስፈላጊ ዝግጅቶችን ለማድረግ ከ 5-7 የስራ ቀናት ይፍቀዱ።

የጥያቄ ሂደት፦

  1. “ይፋዊ” የዲሲ የመንግስት ኤጀንሲ ሰነድ የብሬይል ቋንቋ ትርጉም በ ODR የብሬይል ቋንቋ የትርጉም መጠየቂያ ቅጽ ላይ ጥያቄውን በሚያቀርበው ልዩ ኤጀንሲ መጠየቅ አለበት።
  2. ከደንበኞች/ከሸማቾች በቀጥታ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በይፋዊ የብሬይል ትርጉም መጠየቂያ ቅጽ እንዲቀርቡ ወደ ኤጀንሲው ይላካሉ።
  3. ኤጀንሲ የዋና ሰነዱን በ MS Word ቅርጸት ማቅረብ አለበት። ዋና ሰነዱ በ MS Word ቅርጸት ከሌለ ኤጀንሲው ወደ MS Word ቅርጸት የመቀየር ሃላፊነት አለበት።
  4. የጥያቄ ቅጹን እና የMS Word ሰነዱን ለአካል ጉዳተኛ መብቶች ቢሮ ከሚከተሉት ውስጥ በአንዱ ያስገቡ (የድር ቅጽ ይመረጣል)፦
ኢሜይል፦ [email protected] 
ፋክስ፦ (202) 727-9484
ደብዳቤ፦ 441 4th St., NW, Suite 729 North, Washington, DC 20001
  1. አስፈላጊ ከሆነ ለተጨማሪ መረጃ ODR የኤጀንሲውን ተጠሪ ያነጋግራል
  2. ODR ጥያቄውን ያጸድቃል ወይም ይከለክላል እንዲሁም ለኤጀንሲው ያሳውቃል
  3. ODR ሰነዱ ወደ ብሬይል እንዲተረጎም ያዘጋጃል እና ወደ ጠያቂው ኤጀንሲ ይመልሳል (ከ 5-7 የስራ ቀናት) ።.
  4. ጠያቂው ኤጀንሲ ሰነዱ ለትርጉም እንደቀረበ ለተጠቃሚው/ነዋሪ የማሳወቅ ሃላፊነት አለበት - ሰነዱ ዝግጁ የሚሆንበትን ግምታዊ ቀን እና ሰነዱን ለሚጠይቀው ሸማች/ነዋሪ የሚያገኝበትን ዝግጅቶች ያደርጋል።

ጥያቄዎች አለዎት?

እባክዎ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮን ያነጋግሩ
ዋና ቁጥር፦ (202) 724-5055 ወይም [email protected]

Contact TTY: 
711