Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

odr

Office of Disability Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ውጤታማ ግንኙነት

ውጤታማ ተግባቦት ምንድን ነው?

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ከአካል ጉዳተኞች ጋር ያሉት ተግባቦቶች ከሌሎች ጋር እንዳለው ተግባቦቶች ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ውጤታማ ተግባቦትን ለማረጋገጥ ዲስትሪክቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተገቢውን ረዳት እርዳታዎች እና አገልግሎቶችን መስጠት ይጠበቅበታል። በአካል ጉዳተኛው ግለሰብ የጠየቀው የረዳት እርዳታ ምርጫ በዋናነት ግምት ውስጥ መግባት አለበት። ምንም አይነት አገልግሎት ቢጠየቅ፣ የዲሲ የመንግስት ኤጀንሲ በፕሮግራሙ ላይ መሰረታዊ ለውጥ፣ ወይም ያልተገባ የገንዘብ ወይም የአስተዳደር ሸክም እንደሚያመጣ ካልተወሰነ በስተቀር ለማቅረብ መፈለግ አለበት። የረዳት እርዳታዎች እና አገልግሎቶች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • መስማት የተሳናቸው ወይም መስማት የሚቸገሩ፦ ብቁ ተርጓሚዎች፣ ማስታወሻ ሰሪዎች፣ ቅጽበታዊ መግለጫ ጽሑፎች፣ የጽሑፍ ቁሳቁሶች፣ አጋዥ የማዳመጥ ሥርዓቶች፣ ክፍት ወይም ዝግ መግለጫ ጽሑፎች፣ TTYዎች፣ እና (ተግባቦቱ ውስብስብ ካልሆነ) የጽሑፍ ማስታወሻ መለዋወጥ።
  • ማየት የተሳናቸው ወይም ዝቅተኛ የማየት ዓቅም ያላቸው፦ ብቁ አንባቢዎች፤ ማዳመጫ ቴፕ፣ ብሬይል (የአይነ ስውራን ስርዐተ ጽህፈት)፣ ወይም ትልልቅ የህትመት ቁሶች፣ የፓወር ፖይንት ወይም የቪዲዮ አቀራረቦች የድምጽ መግለጫዎች፤ እና እቃዎችን ለማግኘት እገዛ።
  • የንግግር እክል፦ TTYዎች፣ የኮምፒውተር ተርሚናሎች ((ተግባቦቱ ውስብስብ ካልሆነ) በየተራ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት መተየብ)።

የተቀናጀ ቅንብር ("ማጠቃለል")፦ የዲሲ አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች ከመደበኛ ፕሮግራሞች ሊገለሉ ወይም አገልግሎቶችን እንዲቀበሉ ሊገደዱ አይችሉም። ዲስትሪክቱ አካል ጉዳተኞች ከፕሮግራሞቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እኩል እድል ለመስጠት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የተለየ ወይም ልዩ ፕሮግራሞችን ሊያቀርብ ይችላል። ምሳሌዎች፦

  • የመዝናኛ መምሪያ ተንቀሳቃሽ ወንበር ለሚጠቀሙ ተጠቃሚዎች የተለየ የቅርጫት ኳስ ቡድንን ይደግፋል።
  • አንድ ሙዚየም ዓይነ ስውራን የተወሰኑ ዕቃዎችን ለተወሰነ ጊዜ እንዲነኩ እና እንዲይዙ በመፍቀድ እንዲጎበኙ ያደርጋል (ነገር ግን ዓይነ ስውራንን ከመደበኛው ጉብኝት ማግለል አይችልም)።

የብቁነት መስፈርቶች እና የሕክምና ጥያቄዎች፦ በፕሮግራሞቹ፣ አገልግሎቶቹ ወይም ተግባራቶቹ ውስጥ ለመሳተፍ እንዲህ ያሉ መስፈርቶች የሚያስፈልጉት አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር የዲስትሪክቱ የብቁነት መስፈርቶች አካል ጉዳተኞችን የሚያስወጡ ወይም የማስወጣት አዝማሚያ ሊኖራቸው አይገባም። በፕሮግራሙ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የተጠየቀው እያንዳንዱ መረጃ እንደሚያስፈልግ ካላሳየ በስተቀር አንድ ፕሮግራም የህክምና መረጃ ሊጠይቅ አይችልም።

ደህንነት፦ ዲስትሪክቱ ለአገልግሎቶቹ፣ ለፕሮግራሞቹ እና ለተግባራቱ ደህንነቱ የተጠበቀ አሰራር አስፈላጊ የሆኑ ህጋዊ የደህንነት መስፈርቶችን ሊጥል ይችላል። የደህንነት መስፈርቶች በእውነተኛ ስጋቶች ላይ የተመረኮዙ መሆን አለባቸው እንጂ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የሚደረግ ግምታዊ ትንበያ፣ የጥላቻ ሃሳቦች ወይም በደፈናው የተያዙ አስተያየቶች ላይ መሆን የለበትም።

የዋጋ ጭማሪዎች፦ ምንም እንኳን አቅርቦቶችን መስጠት አንዳንድ ተጨማሪ ወጪዎችን ሊያስከትል ቢችልም፣ ዲስትሪክቱ ወጪዎችን ለመሸፈን በተወሰኑ አካል ጉዳተኞች ላይ ብቻ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርግ
አይችልም። ለምሳሌ፣ መስማት ለተሳነው ሰው ለአስተርጓሚ አገልግሎት፣ ወይም ለአካል ጉዳተኞች ቡድኖች ምንም ተጨማሪ የፕሮግራም ክፍያ ሊኖር አይችልም፣ ነገር ግን የእነዚያን አቅርቦቶች ወጪ ለመሸፈን ለሁሉም ተሳታፊዎች ክፍያዎች ሊጨመሩ ይችላሉ።

የግል አገልግሎቶች እና መሳሪያዎች፦ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ለአካል ጉዳተኞች እንደነዚህ ያሉ አገልግሎቶችን መስጠት በፕሮግራሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች አካል ካልሆኑ በስተቀር በግል
ወይም በግል የታዘዙ መሳሪያዎች (የተሽከርካሪ ወንበሮች፣ የመስሚያ መርጃ መሳሪያዎች ወይም የመገናኛ መሳሪያዎች) የመስጠት ወይም የግል ተፈጥሮ አገልግሎቶችን (ለምሳሌ በመመገብ ፣ በመጸዳጃ ቤት
ወይም ልብስ በመልበስ እገዛ) አገልግሎቶችን የመስጠት ግዴታ የለበትም።

ተደራሽ ባህሪያትን መጠበቅ፦ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የተቋማት የመሳሪያ እና የተደራሽነት ባህሪያት በጥሩ ሁኔታ የሚሰሩ እና ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት። በተደራሽነት ባህሪያት ጥገና እና እድሳት ምክንያት የተገለሉ ወይም ጊዜያዊ መቆራረጦች ተቀባይነት አላቸው::