Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

odr

Office of Disability Rights
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

ADA ርዕስ II

በዲሲ የመንግስት ኤጀንሲዎች የሚቀርቡ ተደራሽ አገልግሎቶችን፣ ፕሮግራሞችን እና ተግባራትን ለመስጠት የሚያገለግል መመሪያ

የ ADA ርዕስ II አጭር መግለጫ ብቁ የሆኑ አካል ጉዳተኛ ግለሰቦች አገልግሎቶችን፣ ፕሮግራሞችን ወይም ተግባራትን ለማግኘት በአካል ጉዳት ምክንያት ከሚደርስ መድልዎ ለመጠበቅ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ላይ የተጣሉትን ግዴታዎች ይመለከታል።

ADA ምንድን ነው?

የ 1990 የአካል ጉዳተኛ አሜሪካውያን ህግ (ADA) አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ግለሰቦች በዘር፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በትውልድ፣ በእድሜ እና በሃይማኖት ላይ ተመስርተው ለግለሰቦች ከሚሰጡት ጋር ተመሳሳይ የሆኑ የሲቪል መብቶች ጥበቃዎችን የሚሰጥ የፌዴራል ሕግ ነው። ADA ለአካል ጉዳተኛ ግለሰቦች በሕዝብ አገልግሎቶች (ለምሳሌ መደብሮች፣ ምግብ ቤቶች እና ሆቴሎች)፣ በሥራ፣ በግዛት እና የአካባቢ መስተዳድር አገልግሎቶች እና በመጓጓዣ እኩል እድል የማግኘት ዋስትና ይሰጣል።

ርዕስ II ምንድን ነው?

ADA እያንዳንዳቸው የተለያዩ የህግ ዘርፎችን የሚዳስሱ አምስት ክፍሎች ወይም "ርዕሶች" አሉት። የ ADA ርዕስ II እንደ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ያሉ የግዛት እና የአካባቢ መንግስታትን ይመለከታል። ርዕስ II ብቁ የሆኑ አካል ጉዳተኞችን አገልግሎቶችን፣ ፕሮግራሞችን ወይም ተግባራትን ማግኘትን በሚመለከት በአካል ጉዳት ላይ ከሚደርስ መድልዎ ይጠብቃል።

ሊታተሙ የሚችሉ ስሪቶች

ማውጫዎች