የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ ህትመት
የ ODR የማህበረሰብ ኑሮ መመሪያ መጽሃፍ እና አብሮት ያለው የማህበረሰብ ኑሮ መርጃ መምሪያ የተዘዋወሩ ሰዎችን ወይም ከተቋማት ወደመረጡት ማህበረሰብ የመዛወር እቅዳችንን ለመርዳት ተገዢ ይሆኑ ቅጾች እና መርጃዎች ስብስብ ናቸው። መመሪያ መጽሃፉ እና መምሪያው የተነደፉት በማህበረሰቡ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ ለመኖር የሚያስፈልጉዎትን አገልግሎቶች እና ድጋፎች ለመለየት እንዲረዳዎ ነው (ሰነዶች ተያይዘዋል)።
የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ (ODR) - One Judiciary Square
441 4th Street, NW
Suite 729 North
Washington, DC 20001
ስልክ፦ (202) 724-5055
TTY: (202) 727-9484
ድረገጽ፦ odr.dc.gov
ሰዓታት፡ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 8፡30 እስከ 5፡30 ከዲስትሪክት በዓላት በስተቀር
ተልዕኮ
የዲሲ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ቢሮ (ODR) ተልእኮ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የሚተዳደሩ ወይም የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው ፕሮግራሞች፣ አገልግሎቶች፣ ጥቅማጥቅሞች፣ ተግባራት እና ተቋማት በአካል ጉዳተኞች ሙሉ በሙሉ ተደራሽ እና ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው። ODR አካል ጉዳተኞችን ለማካተት፣ ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ለመስጠት እና የራሳቸውን እድል በራሳቸው እንዲወስኑ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው። ODR በአካል ጉዳተኛ አሜሪካውያን ህግ (ADA) እንዲሁም በሌሎች የአካል ጉዳተኞች መብቶች ህጎች መሰረት የከተማዋን ግዴታዎች አፈፃፀም የመቆጣጠር ሃላፊነት አለበት።
የ ODR አገልግሎቶች
- መደበኛ ባልሆነ ሁኔታ በመድልዎ ቅሬታዎች የተፈጠረ አለመግባባትን መፍታት
- ስልጠና፣ የቴክኒክ እርዳታ እንዲሁም መረጃ እና ሪፈራል
- ለአካል ጉዳተኞችን የዲስትሪክት ተደራሽነትን ለማሻሻል የፖሊሲ እና የበጀት ምክረ ሃሳቦች።
ይህ መምሪያ በማህበረሰብ ውስጥ ራሳቸውን ችለው ለመኖር ለሚፈልጉ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ነዋሪዎች የሚገኙ በአሁኑ ጊዜ እየሰሩ ያሉ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ መርጃዎች፣ መሳሪያዎች እና ፕሮግራሞች ቅንብር ነው። ከ "የማህበረሰብ ኑሮ መንገድ" መመሪያ መጽሀፍ ጋር በማጣመር ጥቅም ላይ እንዲውል ታስቦ የተሰራ ነው፤ ይሁን እንጂ እንደ መርጃ ዝርዝርም ይሠራል። ይህ ሰነድ መረጃ ሲቀየር ያለማቋረጥ ይዘምናል። ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት እባክዎን ከላይ ያለውን መረጃ ተጠቅመው ቢሯችንን ያነጋግሩ።
ሊታተም የሚችል ስሪት
- የማህበረሰብ ኑሮ መንገድ መርጃ መምሪያ [PDF]
[PDF]ይህ ሰነድ በተንቀሳቃሽ ሰነድ ቅርጸት (PDF) ቀርቧል። ለማየት የPDF አንባቢ ያስፈልጋል። PDF አንባቢ ያውርዱ ወይም ስለ PDFዎች የበለጠ ይወቁ።.
ማውጫዎች
- በግላዊ የአዋቂዎች ግንኙነት ላይ ማስታወሻ
- የእርጅና እና የአካል ጉዳተኝነት መርጃ ማዕከል (ADRC)
- የዓይን መነፅር እገዛ
- አጋዥ ቴክኖሎጂ መርጃዎች
- የግንኙነቶች ማስተላለፊያ አገልግሎቶች
- የባህሪ ጤና የማህበረሰብ መርጃዎች
- የአካል ጉዳተኞች አገልግሎቶች መምሪያ
- የአካል ጉዳተኛ ድርጅቶች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ኤጀንሲዎች
- ለህፃናት የትምህርት መርጃዎች
- የአደጋ ጊዜ የምግብ መደብር እና የምግብ ፕሮግራሞች
- የቅጥር መርጃዎች
- ነጻ የሕክምና ክሊኒኮች
- የልጆች እና የወጣቶች የጤና እና የጉዳይ አስተዳደር አገልግሎቶች
- የቤት ጤና መርጃዎች
- የመኖሪያ ቤት መርጃዎች እና የአደጋ ጊዜ መጠለያ
- መለያ እና የጋብቻ ሁኔታ
- የህግ ጥብቅና መርጃዎች
- የፋይናንስ መርጃዎችን የሚያቀርቡ የአካባቢ መስተዳድር ፕሮግራሞች
- ርካሽ የጥርስ አገልግሎቶች
- የአቻ ድጋፍ እና የባህሪ ጤና አገልግሎቶች
- የግል የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሥርዓቶች (PERS)
- የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች
- ለተመለሱ ዜጎች የሚሆኑ መርጃዎች
- ሰውነታቸው የተቆረጠ ሰዎች አገልግሎት
- የመስሚያ መርጃዎች እና የሌሎች መሳሪያዎች አገልግሎቶች
- የአረጋውያን ዜጋዎች እና የትልልቅ አዋቂዎች አገልግሎቶች
- የማህበራዊ ዋስትና የአካል ጉዳት መድን (SSDI)
- የልዩ ፍላጎት ሃላፊነቶች
- የአደንዛዥ እጽ አጠቃቀም ሕክምና
- ተጨማሪ የደህንነት ገቢ (SSI)
- የትራንስፖርት መርጃዎች
- መገልገያዎች
- የቀድሞ ወታደሮች አገልግሎቶች
- የተሽከርካሪ ወንበር ተደራሽ ታክሲዎች